እንኳን ደህና መጡ!

 • ዉድ ወላጆችና አሳዳጊዎች

  ወደ ቼሪ ክሪክ ትምህርት ቤቶች እንኳን  በደህና መጡ!

   

  ሁሉም ተማሪዎቻችን  ህልሞቻቸው እዉን እንድሆንና   ስኬትን እንድጎነጸፉ   የሚያስችል እጅግ በጣም ጥሩ ትምህርት እንዲያገኙ ለማድረግ እንተጋለን:: የዚህ ተልዕኮ አንዱ  አካል ወላጆች  ልጆቻቸዉን በትምህርታቸው ለመርዳት  የሚያስፈልጋቸውን መረጃዎችን  እንዲያገኙ ማድረግን ይጨምራል።

  የቋንቋ ድጋፍና አገልግሎቶች ቢሮ ተማሪዎችንና ቤተሰቦችን በበርካታ መንገዶች የሚደግፉ የባህል ድጋፍ ሰጪዎችና እና  አስተርጓሚዎች  አሉት ።

  ተግባራቸውና እና ሀላፊነቶቻቸው እነዝህን  ያካትታሉ-

  • በትምህርት ቤት እና በድስትሪክት ስብሰባዎችና ክስተቶች ላይ በመገኘት  የትርጉም አገልግሎቶችን መስጠት
  • ከልጅዎ መምህራንና ከትምህርት ቤቱ ሠራተኞች ጋር እንዲገናኙና እንድተወወቁ መርዳት
  • የትምህርት ቤት ወይንም የድስትሪክት የትምህርት ስርአቶች፤ህደቶች ወይንም በመማር ማስተማር ሥራ ዉስጥ ትምህርት ቤቶች ከወላጆች የምጠብቃቸዉን ሃላፍነቶች በተመለከተ ወላጆች ላሏቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ መስጠት
  • ማንኛዉም የምግባር ወይንም የትምህርት ክትትል( አተንዳንስ ) ጉዳዮች፤የመደበኛ ትምህርት ጉዳዮች፤ ወይንም ሌሎች ጥያቄዎችን በተመለከተ የወላጅ መምህር ስብሰባዎችን ማመቻቸትና የመሳሳሉትን ጉዳዮችን ይፈጽማሉ።

   

  እንዲሁም "Translate" የምለዉን ሜኑ  በመጠቀም ይህ ድረገጽ    ወደ ቋንቋዎ ሊተረጎም እንደሚችል ልናሳውቅዎ እንፈልጋለን ።በቀላሉ ከአርማው ስር የምገኘዉን   “Translate”የሚለውን  ይጫኑ ከዚያም “Google Translate “ የምባለዉን በመጠቀም   ከቋንቋዎች ዝርዝር ዉስጥ የእርስዎን ቋንቋ ይፈልጉ።

   

   ስለ ማናቸውም ሰነዶች ወይም የድረ ገፆች ይዘትን በተመለከተ  ጥያቄዎች ካለዎት ለቋንቋና በህል ድጋፍ ሰጪዎት   መደወል  ይችላሉ።

   

  የባህልና የቋንቋ ድጋፍ ሰጪ  መረጃ

  ተሊሌ ህርጳ - 720-554-5657

  በልጅዎ የትምህርት  ጉዞ ውስጥ እርስዎን ለመደገፍ  በጉጉት እንጠብቃለን  እንደዝሁም  ታላቅ ስኬት እንመኝሎታለን!

  በታላቅ ትህትና

  የቋንቋ ድጋፍና አገልግሎቶች ቢሮ

   

በቴክኖሎጂ እገዛ…

Get In Touch

Last Modified on September 18, 2020