ስለሚቀጥለው የትምህርት ዓመት እቅድ አስፈላጊ መረጃ

 • ውድ የቼሪ ክሪክ ትምህርት ቤቶች ቤተሰቦች
  በሚቀጥለው ዓመት የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን በትምህርት ቤት በአካል የመገኘትና የመማር ዕቅዶችን በተመለከተ አዲስ መረጃ ማጋራት እንፈልጋለን።ለአዳዲስ ምርምር እና ለተለዋዋጭ ሁኔታዎች ምላሽ ለመስጠት የስቴቱ መመሪያ እየተሻሻለ ሲመጣ እቅዶቻችንን እናስተካክለዋለን።
  ዛሬ ከኪንደርጋርተን እስከ 5 ተኛ ክፍል ላሉት ተማሪዎች በሳምንት ለ 5 ቀናት በትምህርት ቤት በአካል በመገኘት የመማር አማራጭን ያካተተ የተሻሻለ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት እቅድን ይፋ አድርገናል ።በእቅዱ ውስጥ እንደ ዋናው ስትራቴጂ ትኩረታችን ተማሪዎችን በቡድን በማደረጀት የአካላዊ ርቀትን መጠበቅን በተቻለ አቅም ሁሉ ስራ ላይ በማወል በኩል የቫይረስ ስርጭቱን ለመግታት ነበር ፡
  ለበለጠ ዝርዝር መረጃ እባክዎን Planning Forward የምባለዉን ድረገጻችንን ይጎብኙ: https://www.cherrycreekschools.org/PlanningForward.
  Planning Forward የሚባለዉን ድረገጽን ለመተርጎም ካለው የቋንቋ አማራጮች ዉስጥ የእርስዎን ቋንቋ ለመግኘት የትርጉም መተግባሪያዉን ይጠቀሙ። እነዝህን መረጃዎችን በተመለከተ ዕገዛ ለማግኘት ከፈለጉ እባክዎን ተሊሌን በዝህ እሜይል ያግኙዋት thirpa@cherrycreekschools.org
  ምንም እንኳን በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች መካከል የምኖረው እንቅስቃሴ ከሁለተኛ ደረጃ ት / ቤቶች የተማሪዎች እንቅስቃሴ ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ልዩነቶች ቢኖሩም ፣ ይህ አካሄድ ከ 6ተኛ እስከ 12 ኛ ክፍል ላሉት ተማሪዎችም በሳምንት እስከ 5 ቀናት ያህል በአካል በትምህርት ቤት የመገኘት እቅድ ለመንደፍ ያስችለናል የሚል እምነት አለን ። በሚቀጥሉት ሳምንታት ዉስጥ በዝህ ጉዳይ ላይ መሥራታችንን እንቀጥላለን እና ልክ እንደተዘጋጁ መረጃዎችን እናቀርባለን።
  በተጨማሪም ፣ ከኪንደረጋርተን እስከ 5ተኛ ክፍል ላሉት ተማሪዎች የሙሉ በሙሉ የኦንላይን ላይ ትምህርትን በመጀመሪያ ደረጃ መርሃ ግብር (Online Elementary program ) አማካይነት እና ለመከከለኛ ደረጃ እና የሁለተኛ ደረጃ ት / ቤት ተማሪዎች ደግሞ Elevation በሚባለው የኦንላይን ትምህርት ቤት አማካይነት ለሁሉም ተማሪዎች የተሟላ የኦንላይን ላይ ትምህርት ዕድሎችን ማቅረባችንን እንቀጥላለን።
  በጁላይ ወር መርሃግብሮችን የሚፈጥሩን ት / ቤቶችን ለመደገፍ የት / ቤታችን ምዝገባ ከጁን 29 እስከ ጁላይ 13 ድረስ ይከፈታል። እስከ ምዝገባው ድረስ እና በምዝገባዉም ወቅት ለቤተሰቦች ማሳሳቢያዎችን መላክ እንቀጥላለን።
  ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በፎል 2020 ወቅት ላይ ስለሚገኙት የአንደኛ ደረጃ ት / ቤቶች እቅዶችን ለመከለስ ወይም ለወደፊቱ አድስ መረጃን ለመከታተል እባክዎን የቼሪ ክሪክን Planning Forward የሚባለዉን ድህረ ገጽን እዝህ ጋ https://www.cherrycreekschools.org/PlanningForward ይጎብኙ ፡
  ከሰላምታ ጋር
  ስካት ስግፍሪድ (Scott A. Siegfried, Ph.D.)
  ሱፐር ኢንተንደንት

Last Modified on June 19, 2020