Translate
I Want To...
- Cherry Creek School District No. 5
- ከቼሪ ክሪክ ትምህርት ቤቶች የተሻሻሉ አስፋላጊ መረጃዎች
Amharic
- ከቼሪ ክሪክ ትምህርት ቤቶች የተሻሻሉ አስፋላጊ መረጃዎች
- ስለሚቀጥለው የትምህርት ዓመት እቅድ አስፈላጊ መረጃ
- ስለ የCCSD የበጀት ተግዳሮቶች አስፈላጊ መልእክት
- ለቀጣዩ የትምህርት ዓመት ስለ የትምህርት አማራጮች አስፈላጊ መረጃ
- ስለሚቀጥለው የትምህርት ዓመት አስፈላጊ መረጃ
- 4-3-2020
- 4-1-2020
- ማርች 17, 2020
- 3-12-2020
- March 9, 2020
- ከፕሪ ስኩል እስከ 12ተኛ ክፍል ላሉት ተማሪዎች በአካል በትምህርት ቤት በመገኘት የመማር መረጃ (In-Person Learning)
- ስለ 2020 ምረቃ አስፈላጊ መረጃ (Graduation Letter)
- ስለ ት / ቤት ኦፊሴሮች በተመለከተ አስፈላጊ መረጃ (SRO Letter)
- የቼሪ ክሪክ ትምህርት ቤቶችን እየገጠመው ስላለው የፋይናንስ ተግዳሮቶች ገለጻ (Budget Video Transcript)
- ስለምርጫ እና ስለ ያለ ክፍያ ቀናቶች የተሻሻለ የበጀት መረጃ ውድ የቼሪ (Budget Furlough)
- የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ከሱፐርተንደንት (Welcome Back)
ውድ የቼሪ ክሪክ ትምህርት ቤቶች ማህበረሰብ
-
በአራፓሆ ካውንቲ ውስጥ የCOVID ሁኔታዎችን መከታተል እንቀጥላለን እናም አሁን ባለው መረጃ ላይ በመመርኮዝ ፣ ኦገስት
(17) በሁለቱም ማለትም በአካል ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ (ይህም ከ K-5ኛ ክፍል ሙሉ ለሙሉ ወደ ትምህርት ቤት
የመመለስ እና ለ ፣ 6-12ተኛ ክፍል ተማሪዎች ደግሞ ቅልቅል ) እና የኦንላይን ላይ አማራጮች ትምህርት ቤቶችን በደህና
የማስከፈት ዕቅዳችንን ወደፊት ለማራመድ ሙሉ ተስፋ አለን። ት / ቤቶችን በደህና ለማስከፈት ውሳኔዎችን ለማድረግ
የሚጠቅሙትን የተወሰኑ የመለኪያዎች መረጃን ለመመልከት አዲሱን የCCSD COVID መከታተያችን በድረ ገጻችን ላይ
ማየት ይችላሉ።. በዚህ ሐሙስ አገስት 6 ላይ የተሻሻለ መረጃን ይጠብቁ።
ለአስተማማኝ የት / ቤት ዳግም መጀመር እቅዳችንን ስንቀጥልም ፣ ከስቴቱ የትምህርት ገንዘብ ድጎማ ባልተለመዱ እና
በአሰቃቂ አደጋዎች ምክንያት እንዲሁም በከባድ ወረርሽኝ ጋር በተዛመዱ የረጅም ጊዜ ወጪዎች ምክንያት የ 60 ሚሊዮን
ዶላር የበጀት ጉድለት ለመቅረፍ እየሰራን እንገኛለን ፡
ዛሬ የበጀት ተግዳሮቶቻችንን ለመጋፈጥ ያለንን ዕቅድን በተመለከተ ለእርስዎ አስፈላጊ የሆነ የተሻሻለ መረጃ አለኝ ፡
ሰኞ ምሽት ላይ ፣ የትምህርት ቦርድ የበጀትና የቦንድ ምርጫ እንዲካሄድ በአንድነት ድምጽ ሰጡ ።በተለይም ቦርዱ በከፍተኛ
ደረጃ ያጋጠመንን የባጀት ጉድለት ለመቅረፍ እና ለስራ ማስኬጃ የ35 ሚሊዮን $ ዶላር ለመሰብሰብ የበጀት ምርጫ ጥሪ
አቅርቧል ። እንደዝሁም ፣ለጥገና፤ ለደህንነት(ጥበቃ) ማሻሻያዎች ፣ እና ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የፈጠራ-ተኮር
ማሻሻያዎችን ጨምሮ የአእምሮ ጤና አጠባበቅ ተቋማትን እና ፣በዲስትሪክቱ ምስራቃዊ ክፍል የተጨናነቁ የመማሪያ
ክፍሎችን ለማቃለል አድስ ትምህርት ቤትን ለመክፈት የሚያስችል ለክፍያ ወጪዎች የምዉል $የ150 ሚልዮን የቦንድ
ምርጫ ጥሪም አቅርቧል ።
ምርጫ እንዲካሄድ ጥሪ የቀረበው ከበጀት ግብረ ሀይል እና ከተመራጮች ምክር ቤት ፣ ከወላጆች ፣ ከመምህራን ፣
ከአስተዳዳሪዎች ፣ ከድስትርክቱ ሠራተኞች ፣ ከተማሪዎች እና ከማህበረሰቡ አባላትን ያቀፈ ሁለት የበጎ ፈቃደኛ ኮሚቴዎች
ነው።እነዝህ ቡድን አዳድስ የገቢ ምንጮችን እና ከባባድ ቅነሳዎችን ለማድረግ ለወራት ስሠባሰቡና ስወያዩ ነበር። ይህ ዉሳኔ
100,000 ዶላር የምያወጣ ቤት ላላቸው የቤት ባለቤቶች ላይ የሚያመጣው አጠቃላይ ተፅእኖ በወር $ የ1.65 ዶላር
ክፍያን በቤት ወጪያቸው ላይ ይጨምራል።
ስለ የበጀት እና የቦንድ ምርጫ ፓኬጅ እንዲሁም የበጀት ተግዳሮቶቻችንን በተመለከተ ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት
ይጠብቁን። የበጀት ሁኔታችን እጅግ በጣም አስቸጋሪ ቢሆንም ፣ ለሁሉም ተማሪዎች ጥሩ ትምህርት እና ብሩህ የወደፊት
ተስፋ የሚሰጥበት መንገድ ለመግኘት ከህብረተሰቡ ጋር በህብረት መስራት እንደምንችል እርግጠኛ ነኝ ፡
ስለ ት / ቤት ዳግም መጀመር የቅርብ ጊዜ መረጃ ለማግኘት Planning Forward 2020-2021ድረገጽን ይጎብኙ
እንደዝሁም በዚህ ሐሙስ ላይ የተሻሻለ መረጃን ለማግኘት ይጠብቁ።
Planning Forward የምባለዉን ድረ ገጽ ለመተርጎም ፣ በጥቁር መስመሩ ውስጥ ያለዉን translate የምለዉን የቋንቋ
መራጩን ይጠቀሙ። ፤እነዝህን መረጃዎችን በተመለከተ በቋንቋዎ ዕገዛን ለማግኘት ከፈለጉ እባክዎን ተሊሌን በዝህ እሜይል
ያግኙዋት thirpa@cherrycreekschools.org
የሠመር እረፍቱን በመልካም ጤንነት እያሳለፉ እንደሆነ ተስፋ አደርጋለሁ
በታላቅ ትህትና
ስካት ስግፍሪድ (Scott A. Siegfried, Ph.D.)
ሱፐር እንተንደንት